17/05/2026
የአማራ ክልል ከፍተኛ መሪዎች የአዋሽ፣ ኮምቦልቻ፣ ሃራ ገበያን የባቡር ፕሮጀክት ዳግም ሥራ አስጀመሩ።
*****
392 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር መንገድ ፕሮጀክቱ 2007 ዓ.ም ተጀምሮ እስከ 2012 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቅ ነበር። ኾኖም በሰሜኑ ጦርነት በደረሰበት ውድመት እና ዘረፋ ምክንያት ለመገባደድ ተቃርቦ የነበረው ፕሮጀክት ተስተጓጉሎ ቆይቷል።
ይህ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ፕሮጀክት መጠናቀቅ የንግድ ሥርዓቱን በማሳለጥ፣ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። የባቡር መስመሩ በኤሌክትሪክ ኀይል የሚሠራ ነው።
የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።