Construction in Ethiopia

Construction in Ethiopia Providing construction information for free for more http://constructioninethiopia.com
also join us on telegram

This web site will provide reliable packages of data, information, news, formats, estimates, current construction material cost and also helps to connect with experts practicing in the construction sector. In this free web site one can register as Contractor, Consultant, Supplier or as a construction personnel (as a Project Manager, Construction Engineer, Contract Engineer, Design Engineer, Site o

r office Engineer, As Forman, Equipment Operator, Driver..). join us on telegram t.me/constructionproxy

 #ጥቆማየኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል።የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ...
28/05/2026

#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን የነጻ ትምህርት ዕድል ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ኒውክሊየር ኃይል ኮሚሽን ጠንካራ ሀገራዊ የኒውክሊየር መሰረተ ልማት ለመገንባት የሚያስችሉ ከፍተኛ ባለሙያዎችን ለማፍራት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ሰልጣኞች በሩሲያ የነጻ ትምህርት ዕድል ማመቻቸቱን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ ለ2026/27 የትምህርት ዘመን በሩሲያ በሚገኙ ስመጥር የሳይንስና የምህንድስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ብቁ አመልካቾች እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

የሚሰጡ የትምህርት ዘርፎች በኒውክሊየር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ሲሆን እነዚህን ዘርፎችንም ያካትታል ፡-
- Nuclear Power Engineering and Heat Physics (BSc & MSc)
- Nuclear Physics and Technology (BSc)
- Nuclear Power Plants Design, Operation and Engineering (BSc)
- Heat Power Engineering (BSc)
- Management in Technological Systems (MA)

የመወዳደሪያ መስፈርቶች ?

• ለመጀመሪያ ዲግሪ (BSc) ዕድሜያቸው ከ20 ዓመት ያልበለጠ እና የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ አማካኝ ውጤታቸው 500 እና ከዚያ በላይ የሆነ።

• ለሁለተኛ ዲግሪ (MSc/MA) ዕድሜያቸው ከ30 ዓመት ያልበለጠ እና በሳይንስና ምህንድስና ዘርፍ በከፍተኛ ውጤት የተመረቁ።

ሴት አመልካቾች ለዘርፉ እንዲበረታቱ ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል።

መስፈርቱን ምታሟሉ አመልካቾች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት 5 የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን እና ደጋፊ ሰነዶቻችሁን በPDF በማዘጋጀት በኮሚሽኑ የኢሜል አድራሻ [email protected] መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ/ም
Via tikvahethiopia

28/05/2026

Head, Building Maintenance Section 🏢
Hibret Bank S.C.

Job Overview
Salary Offer: As per Company Scale 💰
Experience Level: Junior
Total Years Experience: 2
Date Posted: May 24, 2026 📅
Deadline Date: May 30, 2026 ⏳

Job Requirement
Educational Qualification: BSc in Electrical Engineering ⚡ / Mechanical Engineering ⚙️ / Civil Engineering 🏗️ or Construction Technology Management
Work Experience: 4 years as Senior Building Maintenance Engineer or equivalent, or 9 years relevant experience in the banking industry 🏦
OR
2 years as Head, Building Maintenance Section or equivalent, or 10 years relevant experience
Salary: As per the Bank’s Salary Scale 💵
Place Of Work: Head office 🏢

How to Apply
https://t.me/constructionvacancies

 #ዜና| አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና እንዲወስዱ ሊገደዱ ነውአሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች ሰልጥነው የብቃት ምዘና እንዲወስዱ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡...
28/05/2026

#ዜና| አሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና እንዲወስዱ ሊገደዱ ነው

አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች ሰልጥነው የብቃት ምዘና እንዲወስዱ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ሊዘረጋ ነው፡፡

ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል ያለው የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ነው፡፡

ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፣ የምዘና ሂደቱ በዲጂታል ሲስተም እንዲመራ ተደርጎ ተቀርጿል ሲል ሚኒስቴር መ/ቤቱ መባህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መገለጫ ላይ ጠቅሷል ።

አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና ይወስዳሉ ተብሏል ።

በዚሁ መሰረት ይህንን ሀገራዊ ፕሮጀክት በይፋ ወደ ትግበራ ለማስገባት በተለይም አጠቃላይ የአሽከርካሪዎች ምዝገባ እና ስልጠና በተመለከተ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከኤስ ዲ ኤስ ሴፍቲ ኤንድ ድራይቪንግ ስኪልስ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችለውን የስራ ውል ስምምነት መፈረማቸው ተሰምቷል።

በመሆኑም ይህ "ሀገር አቀፍ የአሽከርካሪዎች የብቃት ምዘና፣ የስልጠና እና የደህንነት ማሻሻያ ፕሮጀክት" የመንገድ የትራፊክ ደህንነትን በማጠናከር ረገድ የጎላ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ተገምቷል፡፡

ማናቸውም አሽከርካሪዎች በሙሉ አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት ይዘረጋል ተብሏል።

ይህ አሰራር የመንገድ ደህንነትን በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ዜጎቻችን ብሎም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች በመንገድ የትራፊክ አደጋ ምክንያት ሞትና የአካል ጉዳት እንዲሁም የንብረት ውድመት ለመቀነስ ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያበረክት መሆኑ ከፍተኛ እምነት ተጥሎበታል።

በመሆኑም ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ሁሉም ዝግጁ እንዲሆን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳስቧል።

ምንጭ:- ሸገር ራዲዮ

ሐዋሳ ያላችሁ 👇👇👇
28/05/2026

ሐዋሳ ያላችሁ 👇👇👇

ባለሙያዎች ሴራሚክ ላይ ሌላ ሴራሚክ ይደርባል ዎይ?
28/05/2026

ባለሙያዎች ሴራሚክ ላይ ሌላ ሴራሚክ ይደርባል ዎይ?

ሲኖ ትራክ ያላችሁ - Type: Sino Truck / Dump truckmodel:  - Year : 2012 and above - Location: Bishofitu Airport ዋናው ግቢ - Price:...
28/05/2026

ሲኖ ትራክ ያላችሁ
- Type: Sino Truck / Dump truck
model:
- Year : 2012 and above
- Location: Bishofitu Airport ዋናው ግቢ
- Price: 1,200 Birr በሰዓት (before VAT)
- በቀን ከ 10 -16 የስራ ሰዓት
- Advance : 1 month

Contact: telegram at 👇👇👇

27/05/2026
ግንቦት 19/2018በደርግ ዘመነ መንግሥት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመምራት የሚታወቁት አቶ ካሳ ገብሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አቶ ካሳ በ92 ዓመት እድሜያቸው ይኖሩበት በነበረው አሜ...
27/05/2026

ግንቦት 19/2018

በደርግ ዘመነ መንግሥት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመምራት የሚታወቁት አቶ ካሳ ገብሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

አቶ ካሳ በ92 ዓመት እድሜያቸው ይኖሩበት በነበረው አሜሪካ ሀገር ህይወታቸው ያለፈው በዛሬው እለት ነው።

ኢንጂነር ካሳ ገብሬ ከኢትዮጵያ ህንፃ ኮሌጅ በሲቪል ምህንድስና ካናዳ ሀገር በሚገኘው የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ዓመት የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

በትምህርት ሚኒስቴር በዋና መሃንዲስነት፣ በቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርነት፣ በኤርትራ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና መሃንዲስ፣ በሕንጻ ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት እና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነቶች እስከ ደርግ ስርዓት ማብቃት ድርስ አገልግለዋል።

ኢንጂነር ካሳ በደርግ ስርዓት ወቅት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችንም መርተዋል።

በሶማሌ ወረራ ጦርነት ወቅት ህዝባዊ ሠራዊት የሰለጠንበትን የታጠቅ ጦር ሜዳ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማዘጋጀታቸው ከሚጠቀስላቸው ስራዎቻቸው መከከል ይገኝበታል።

የጀግኖችና ህፃናት አምባ ምስረታዎች ወቅት የግንባታ ዘርፉን መርተዋል።

የጣና በለስ ግድብ፣ የቀይ መስቀል ሕንጻ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ፍልውሃ ሕንጻዎች፣ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን፣ በርካታ የከተማ ፕላኖችና ድልድዮች ከታላላቅ ሥራዎቻቸው መካከል ይጠቀሳሉ።

በዚህም ጉልህ አስተዋጿቸው ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ከመሠረት ጣዮች መካከል አንዱ ተደርገውም ይነሳሉ።

አገሪቷ ከፍተኛ የድርቅ አደጋ ውስጥ በገባችበት ወቅትም ዜጎችን ድርቅ ካለበት ወደ ድርቅ ወደሌለበት አካባቢ በማዛወር ከእልቂትና ከረሃብ አደጋ በመታደግ ትልቅ ሰብዓዊ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውምን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ኢንጂነር ካሳ በኢህአዴግ መንግሥት ዘመን 12 ዓመት ከ3 ወር ታስረዋል።

ከእስር ከተፈቱ በኋላ አብዛኛውን ኑሯቸውን ያደረጉት በአሜሪካ ሀገር ሲሆን መጽሐፍ ጽፈው አጠናቅቀው፣ ግን ለሕትመት ሳይበቃ አረፈዋል።

አቶ ካሳ ገብሬ የሁለት ወንዶች እና የሁለት ሴቶች ልጆች አባትም ነበሩ።

በ92 ዓመት እድሜያቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ኢንጂነር ካሳ ገብሬ የቀብር ስነስርዓታቸው በአሜሪካን ሀገር ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኘው ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል፣ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓም፣ በአገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ በ3:30 ሰዓት የሚፈፀም ሲሆን በአዲስ አበባ የመታሰቢያ መርሃግብር በቀጣይ ቀናት ይደረግላቸዋል ተብሏል።

የርሰዎ ምርጫ ምን ነበር?
27/05/2026

የርሰዎ ምርጫ ምን ነበር?

" ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ ይደረጋል " - ሚኒስቴሩ"የመንገድ  የትራፊክ አደጋን ለመግታት" አሽከርካሪዎች በዘመናዊ አሰራር ብቃታቸው እንደገና ሊመዘን እንደሆነ...
27/05/2026

" ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ ይደረጋል " - ሚኒስቴሩ

"የመንገድ የትራፊክ አደጋን ለመግታት" አሽከርካሪዎች በዘመናዊ አሰራር ብቃታቸው እንደገና ሊመዘን እንደሆነ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አሳወቀ።

ሚኒስቴሩ፤ " አሁን በስራ ላይ ያሉ ሁሉም አሽከርካሪዎች እንደገና እንዲሰለጥኑና እንዲመዘኑ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችል አጠቃላይ የሰነድ ዝግጅት ተጠናቋል " ብሏል።

" ይህ አዲስ አሰራር ከተለመደው አሰራር በተለየ መልኩ ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንደሆነና የምዘና ሂደቱ ከእጅ ንክኪ (የሰው ጣልቃገብነት) የጸዳ እንደሆነ " አመልክቷል።

አሽከርካሪዎች ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ቅድሚያ ስልጠና እንደሚወስዱና ከመጀመሪያው ምዝገባ ጀምሮ እስከ ስልጠናው ብሎም ምዘናና ሰርተፊኬሽን ድረስ ያለው አጠቃላይ ሂደት በዘመናዊ ሲስተም እንደሚመራ ነው ሚኒስቴሩ ያመልከተው።

ይህን ስራ ለመስራት ሚኒስቴሩ SDS Safety & Driving Skills ከተባለ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጋር የስራ ውል ስምምነት መፈረሙን አሳውቋል።

ሁሉም አሽከርካሪዎች አዲሱን የብቃት ምዘና በመውሰድ እና በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ብቃታቸውን በተጨባጭ በማረጋገጥ ብቻ እንዲያሽከረክሩ የሚያስገድድ ዘመናዊ የቁጥጥር ሥርዓት እንደሚዘረጋም ተነግሯል።

ሚኒስቴሩ " ሁሉም አሽከርካሪ በዚህ ሂደት የሚያልፍ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ለዚህ ዙር በቅድሚያ ማንኛውም የንግድ ተሽከርካሪ የሚያሽከረክር አሽከርካሪ የምዝገባና የስልጠና እንዲሁም የምዘና ሂደቱ በቅርቡ ስለሚጀመር ዝግጁ እንዲሆን " ሲል አሳስቧል።

Via ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
ግንቦት 18 ቀን 2018 ዓ/ም

Address

Cmc Road
Addis Ababa
10338

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Construction in Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Construction in Ethiopia:

Share