COTM Community in Wolaita sodo university

COTM Community in Wolaita sodo university Every one must have known about construcation!

ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ይፋ አደረገ።  --------------------------------------------------------------...
27/02/2024

ዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ይፋ አደረገ።
-------------------------------------------------------------------
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት አክበር ጩፎ (ዶ/ር ) የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እንዲሁም በተከታታይ የትምህርት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ጠቅላላ ተማሪዎች 312 ያህሉ የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ብቁ ሆነው መመዝገባቸውን ምክትል ፕሬዝዳንቱ አሳውቀዋል።

በዩኒቨርሲቲው በአስራ ሁለት የትምህርት መስኮች የተሰጠውን የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና በአጠቃላይ 312 ተማሪዎች መውስዳቸውንም ዶክተር አክበር ጠቁመዋል።

በመውጫ ፈተናው ከተቀመጡ ጠቅላላ ተማሪዎች በድምሩ 78.72 በመቶ ማለፊያውን ነጥብ ማስመዝገባቸውንም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ተገቢውን ሁለንተናዊ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ፈተናውን ማስፈተን ችሏል ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ ፤ በሂደቱም የከፋ ችግር አላጋጠመንም ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ለመጀመሪያ ግዜ ከተካሄደው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና አንጻር እንደ ተቋም በ2016 ዓ.ም አጋማሽ መውጫ ፈተና የተሻለ አፈጻጸም ታይቷል ሲሉም ዶክተር አክበር ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የ2016 ዓ.ም አጋማሽ መውጫ ፈተና በጤና ሳይንስና ሕክምና ኮሌጅ በተለያዩ የጤና ፕሮግራሞች (Medical laboratory 100%, Public health 100%, Midwifery 100%, Nursing 100% እና Pharmacy 97%) ተፈታኞች እጅግ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸው ለአብነት ተጠቃሽ መሆኑንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

በቀጣይ ግዜያት ያጋጠሙ ችግሮችን በጥልቀት በመገምገም፣ ተገቢውን የእርምት እርምጃ በመውሰድ እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት በሁሉም ኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት እንሰራለን ብለዋል።

ዶክተር አክበር በመውጫ ፈተናው ማለፊያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉት ሲሆን ፤ የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ተማሪዎች ቀጣይ ሰኔ ወር መጨረሻ ፈተናውን ዳግም መውሰድ የሚችሉ መሆኑንም አሳውቀዋል።

የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና የከፋ ችግር ሳያጋጥም እንዲሳካ ድጋፍ እና ክትትል ያደረጉ አስተባባሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትንም ምክትል ፕሬዝዳንቱ አመስግነዋል።

የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከዛሬ የካቲት 18/ 2016 ዓ.ም ጀምሮ ስለተለቀቀ ተፈታኞች በ https://result.ethernet.edu.et ሊንክ ማየት የሚችሉ መሆኑንም አሳውቀዋል።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

📷የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት!!

➤ የካቲት 18 /2016 ዓ.ም (ወሶዩ)

◼ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟላ መረጃ ለማግኘት ትክክለኛውን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ🔻

▪Telegram ➲ https://t.me/WolaitaSUniversity

▪Facebook ➲ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063820159424

▪YouTube ➲ https://www.youtube.com/channel/UC6VukdZbl5iVgZGXG8BkMdw/videos

Website ➲ http://www.wsu.edu.et/

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን🙏🙏

01/10/2019

በዩኒቨርሲቲያችን የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ከ20-21/01/2012 ዓ.ም ድረስ እንደሚካሄድ ማስታወቃችን ይታወሳል።

የምዝገባ ሂደቱንም ለማቀላጠፍ ይቻል ዘንድ ምዝገባው በየኮሌጆችና ትምህርት ቤቶች እንደሚሆንም ጠቁመናል።

በዚሁ አግባብ ለምዝገባው አመቺነት እንዲረዳ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት በገጹ የለጠፈውን የምዝገባ ቦታ ጥቆማ እንድታውቁት ከታች ለጥፈነዋል፤ አንብበው ለሌሎች ያጋሩት።

01/12/2018

👋 ስላም እንዴት ናቹ ደና እንደሆናቹ ተስፋ አደርጋለሁ::

ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች
06/11/2018

ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች

I'll like to say hi for all member'scotm
28/10/2018

I'll like to say hi for all member's
cotm

15/10/2018
14/10/2018

መልካም የትምህርት ዘመን ያድርግላችሁ ።

በተለይ ለአዲስ ገቢዎች 👆

NB አሰታየት ወይም ጥያቄ ካላቹ መጠየቅ ይቻላል ።

"ለተሻለ ለወጥ አብሮ መሰራት"

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when COTM Community in Wolaita sodo university posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to COTM Community in Wolaita sodo university:

Share