17/05/2026
«የጭስ አልባ ከሰል ፈጠራ አሸናፊው ወጣት እዮብ አለሙ እና የ«ብሩህ አዲስ 3» ስኬት»
🇪🇹 ግንቦት 9/2018 ዓ.ም 🇪🇹
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆነው ወጣት እዮብ አለሙ በውስጡ የነበረውን የፈጠራ ኃሳብ ወደ ተጨባጭ ሥራ በመቀየር ዛሬ ላይ የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ስኬታማ ወጣት ነው።
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አዘጋጅነት በተካሄደው «ብሩህ አዲስ 3» የንግድ ሥራ ኃሳብ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበረው እዮብ አካባቢን የሚጠብቅና ለጤና ተስማሚ የሆነ የፈጠራ ሥራ ይዞ በመቅረብ አሸናፊ መሆን የቻለ ወጣት ነው።
ይህ እዮብ የተሳተፈበት የ"ብሩህ አዲስ" የንግድ ሥራ ኃሳብ ፈጠራ ውድድር በአዲስ አበባ ከተማ በየዘርፉ የሚታዩ ቁልፍ ችግሮችን ለመፍታትና የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚችሉ አዳዲስ ኃሳቦች ይዘው የሚመጡ ወጣቶችን ለማበረታታት የተዘጋጀ መርሃ ግብር ነበር።
የፈጠራ ኃሳቡ መነሻና ማህበራዊ ፋይዳው
ወጣት እዮብ ወደ ጭስ አልባ ከሰል ማምረት ስራ እንዲገባ ያደረገው ዋነኛ ምክንያት። እዮብ በሚኖርበት አካባቢ ሦስት ልጆችን የምታስተዳድርና ቡና በማፍላት የምትተዳደር አንዲት እናት ነበረች። ለዚህች እናት የዕለት ተዕለት ሥራ ትልቅ ወጪና ጫና እየሆነባት የመጣውን የከሰል ወጪ የሚቀንስና ጤናዋን የማይጎዳ አማራጭ ነገር ምን መፍጠር ይቻላል በሚል ጥናት በመጀመር ለዛሬው ስኬቱ መሠረት ጣለ።
ይህ ችግር ፈቺ የፈጠራ አካሄድ የውድድሩን መሠረታዊ ፍልስፍና ሙሉ በሙሉ የሚያንጸባርቅ ነው ምክንያቱም "ብሩህ አዲስ" ወጣቶች ዕውቀትና ክህሎታቸውን መሠረት አድርገው የማህበረሰብንና የተቋማትን ችግሮች የሚፈቱ ሀሳቦችን በማፍለቅ ወደ ንግድ እንዲቀይሩት ማገዝን ዓላማ ያደረገ በመሆኑ ነው ።
የጭስ አልባ ከሰል አሰራር ሂደት
የከሰሉ አሰራር ሂደት ሙሉ በሙሉ የአካባቢን ተረፈ ምርት ጥቅም ላይ የሚያውልና ብክለትን የሚከላከል ነው። እዮብ ግብዓቱን ከተለያዩ የእንጨት ቤቶች የሚወጡ ተረፈ ምርቶችን በመሰብሰብ የካርቦናይዝ የማድረግ ሥራ ይሰራል።
በመቀጠልም ከተዘጋጀው ስታርች ጋር በማደባለቅ፣ በሞልዲንግ ማሽን አማካኝነት የሚፈለገውን ቅርፅ እንዲይዝ ያደርጋል። ይህ ምርት ረጅም ሰዓት የመቆየት አቅም ያለውና በፍጹም ጭስ አልባ በመሆኑ ለቤት ውስጥ አገልግሎት እጅግ ተመራጭ ነው።
እዮብ ስለ "ብሩህ አዲስ 3 የንግድ ሥራ ኃሳብ ፈጠራ ውድድር" መረጃ አግኝቶ በወረዳ ደረጃ ከተመዘገበ በኋላ፣ በክፍለ ከተማው 1ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ መሆን ችሏል። ክፍለ ከተማውን በመወከል ወደ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የተሸጋገረው እዮብ የ100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ሽልማትና የእውቅና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል።
በመቀጠልም በፌደራል ደረጃ በደብረዘይት ከተማ በተዘጋጀው የተወዳዳሪዎች የተጠናከረ የስልጠና ካምፕ ላይ ተሳትፏል።
እጅግ በርካታና ጠንካራ የፈጠራ ኃሳቦች በነበሩበት በዚህ ውድድር ላይ እዮብ የፈጠራ ስራውን በሚገባ በማስረዳት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመረጡት "ቶፕ 100" ምርጥ አሸናፊዎች ተርታ ውስጥ መግባት ችሏል።
ይህ የእዮብ የውድድር ጉዞ ብሩህ አዲስ የንግድ ኃሳብ ፈጠራ ውድድር ላይ የተቀመጡትን ሦስት የድጋፍ ማዕቀፎች ማለትም ማሰልጠን ፣ መሸለም እና ማብቃት በተግባር ያሳየ ነው ።
ወጣቱ የ"ብሩህ አዲስ 3" ውድድርን በስኬት ካጠናቀቀ በኋላ ኃሳቡን ወደ ሰፊ ንግድ ለመቀየር ትልቅ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የገጠመው ትልቁ ፈተና የማምረቻ ቦታ እጥረት ነው። ፈጠራው በሰፊው ውጤታማ እንዲሆን ሰፊ ቦታ የሚጠይቅ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የማምረ