Wedaju Orkaido

Wedaju Orkaido Engineering and Technology navigator

መዉቀስና ግለሰባዊ እድገት“ሌሎችን የሚወቅስ በእድገት ጉዞው ረጅም መንገድ ይቀረዋል። እራሱን የሚወቅስ በግማሽ መንገድ ላይ ነዉ፣ ማንንም የመይወቅስ ከግቡ ደርሷል።”                ...
26/08/2025

መዉቀስና ግለሰባዊ እድገት
“ሌሎችን የሚወቅስ በእድገት ጉዞው ረጅም መንገድ ይቀረዋል። እራሱን የሚወቅስ በግማሽ መንገድ ላይ ነዉ፣ ማንንም የመይወቅስ ከግቡ ደርሷል።”
....ቻይናውያን......

14/08/2025

ነቀፋ ጠቃሚ ምክር ነዉ !!!
**********************
ነቀፋና ትችት ለብዙዎቻችን ምቾት የሚሰጥ ባይሆንም በሰለጠነ መንገድ ካየነዉ ደግሞ ጠቃሚ መረጃና ወቅታዊ ምክር ነዉ::

በሠራንባቸዉ ችግር ፈቺ ሥራዎች ስንሞገስ እንዲሁም በተሳሳትንባቸዉ ጉዳዮች ደግሞ ስንነቀፍና ስንተች ሚዛናዊ ሆነን መዉሰድ ብስለትም ይሆናል::

መነቀፍንና መተቸትን አዎንታዊ በሆነ መንገድ በመቀበል: በማጥራት: በማረምና ተግባራዊ ምላሽ እየተሰጠ ወደ ፍት መሄድ ሲገባን ቁጭ ብለን በቃላት መተኳኮስ ጊዜ ማጥፋት ተገቢ አይሆንም::

እዉነትን በእምነት መግለፅና ዉሸትን በድፍረት መሟገት የነቀፋ እና የትችት ሚዛን የሚያስተካክል ስለሆነ በእኛ በኩል በዋናዉ ተልዕኳችን ላይ ብቻ በማተኮር መሥራት ይበጀናል::

ከነቀፋና ከትችት ለማምለጥ ተብሎ ነባራዊ ሁኔታዎችን በአድርባይነት ማለፍና መታለፍ ሳይሆን በሚቻለን ሁሉ ለሕዝባችን ጠንካራ አንድነት እና ለሁለንተናዊ ብልፅግናችን በትጋት መሥራት ቀዳሚ ተግባር ቢሆን ይመረጣል::

ሰዋዊዉ ባህሪያችን በነቀፋና በትችት እንዲሁም በሙገሳና በምስጋና የታጀበ በመሆኑ ሁሉንም ያለ ልዩነት ከመስማት ባሻገር አልወደዱንም ብለን መነቋቆር እና ድጋፍ አለን ብለን መወገንም ጠቃሚ አይሆንም::

ብዙዎች ስለወደዱን በጅምላ ይወዱናል ደግሞም ብዙዎች ስለጠሉን ሰማይ ምድሩ ይጠላናል ማለትም አይደለም:: ሁሉም በልኩ ስለሆነ ሚዛናዊ መሆንን መልመድ ጠቃሚ ይመስለኛል::

የእኛ ትዉልድ በአብዛኛዉ ሲወደንም ይሁን ሲጠላን ሚዛናዊነት የሚጎድለዉ በመሆኑ በእኛ በኩል ነቀፋና ትችት እንደ መረጃና ጠቃሚ ምክር በመዉሰድ በገባን እና በተረዳን መጠን የተቻለንን ሁሉ በማድረግ ኃላፊነታችንን በቅንነትና በታማኝነት መወጣት እንዳለብን ይሰማኛል::

የባዛር ጥሪ ስለማስተላለፍ ይሆናል የተከበራችሁ መላው የኮንሶ ዞንና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ከሁሉም በማስቀደም እንኳን ለዚህ ታላቅ ታርካዊ  ሥራ የሚንሰራበት ዕለት ዋዜማ  በሰላም አደረሰን...
13/08/2025

የባዛር ጥሪ ስለማስተላለፍ ይሆናል

የተከበራችሁ መላው የኮንሶ ዞንና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ ከሁሉም በማስቀደም እንኳን ለዚህ ታላቅ ታርካዊ ሥራ የሚንሰራበት ዕለት ዋዜማ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ

በኮንሶ ዞን የካራት ዙሪያ ወረዳ ለትውልድ የሚበቃ ተግባር ለመፈጸም ሁሉም የህብረተሰብ አካል በከፍተኛ ተሳትፎ በመሳተፍ እንቅስቃሴ ሰፊ ሥራዎችን ለመስራት ባዛር ከነሐሴ 17-18/2017 ዓ/ም ተዘጋጅቷል።

ካራት ዙሪያ ወረዳ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ መስህቦች እጅግ የበለጸገ ወረዳ ሲሆን በተለይም ኦሶማታ ቱሮ ፣ የጎሣ መኖሪያ ድንቅ የባህል ጥብቅ ደኖች ዘመን የማይሽራቸው የተፈጥሮ ድንቅ ሀብቶች በዩኒስኮ የተመዘገቡ ባህላዊ አምባ መንደራት ቡሶ፣ መጨሎ፣ ጎጫ አምባ መንደራት የሶሮቦ የአርክዮሎጅ ሳይት እንዲሁም በርካታ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መገኛ እንዲሁም እምቅ የጤፍ ፣ የማዕድን፣ የታታሪ አርሶ አደር መገኛ ቦታ ስሙ አሁንም ደምቆ ይታያል።

በዘንድሮ 2017 ዓ/ም ከኪራይ ቤት ለመዉጣት የ32 ክፍሎች ግንባታዉን ለማጠናቀቅ የተያዘዉን ዕቅድ ለማሳካት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማሳካት የሁላችንም ርብርብ ይጠይቃል።

በግንባታው ላይ አሻራዎን ለማሳረፍ ከዚህ በታች በተቀመጠው አካውንት ገቢ ማድረግ ይችላሉ፦

✍️ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000709734532✍️

✍️አዋሽ ባንክ - 013250182168800 ✍️

ይህንን ጠቃሚ የልማት ፕሮጀክት ለመደገፍ እና ወረዳው በአስቸኳይ ከኪራይ ወጪ እንዲላቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የወረዳው አስተዳደር ጥሪውን አቅርቧል።

የካራት ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
የተከበሩ አቶ ኩሴ ጅሎ

ሼር በማድረግ ለታላቅ አሻራ ሥራ ተባበሩ!!

03/08/2025
11/12/2024
የሰማዩ አምላክ በባለጠግነቱ  እንድህ አንበሽብሾናል።
09/11/2024

የሰማዩ አምላክ በባለጠግነቱ እንድህ አንበሽብሾናል።

02/11/2024

interiour decoration!

.........ላልተጠበቀው ነገር መዘጋጀት.........ሁል ጊዜ አንድን ነገር ስትጀምሩ በመንገድህ ላይ ያልተጠበቀ ነገር እንደሚገጥማችሁ አትዘንጉ፡፡ እነዚህ የማትጠብቋቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ...
02/11/2024

.........ላልተጠበቀው ነገር መዘጋጀት.........

ሁል ጊዜ አንድን ነገር ስትጀምሩ በመንገድህ ላይ ያልተጠበቀ ነገር እንደሚገጥማችሁ አትዘንጉ፡፡ እነዚህ የማትጠብቋቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ ምንጫቸው ከእናንተ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ነገሮች ናቸው፡፡ ሊገመት የማይችል የሁኔታዎች መለዋወጥ፣ ሊተነበይ የማይችል የሰዎች ባህሪይ መቀያየርና የመሳሰሉት ሁኔታዎች ከመንገዳችሁ ላይ እንቅፋት እንዳይጠፋ ያደርጉታል፡፡

እነዚህ ሁኔታዎች አንድን ነገር ለመጀመር፣ ከጀመርን በኋለ ለመቀጠል፣ አልፎም ወደፍጻሜ ስንደርስ እንዳንጨርስ ሲጋረጡብን እናገኛቸዋለን፡፡ ይህንን አይነቱን የማይቀር የሕይወት ሂደት የተለያዩ ሰዎች በተለያየ መልኩ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ አንዳንዶች ለደረሰብን እንቅፋት ሁሉ በሰዎች፣ በሁኔታዎችና በፈጣሪ የማማረር ልማድ ልማድ አለብን፡፡ በዚያም ሁኔታ ተደብቀን በተስፋ መቁረጥ እርምጃችንን እንተዋለን ወይም ለሌላ ጊዜ እናስተላልፈዋለን፡፡

ሶስት አይነት እንቅፋቶች አሉ . . .

1. አንዳንዱ እንቅፋቶች ቀድሞውን ሊደርሱ የሚችሉ እንቅፋቶችን በማጤንና በማቀድ ልታስወግዷቸው የምትችሏቸው ናቸው፡፡

2. ሌሎቹ እንቅፋቶች አስቀድማችሁ አቀዳችሁም አላቀዳችሁም ከመምጣት የማታስወግዷቸው እንቅፋቶችና እንደአመጣጣቸው ልትመልሷቸው የምትችሏቸው ናቸው፡፡

3. ሌሎቹ ግን እንቀፋቱና ችግሩ እያለ መንገዳችሁ ላይ ብቻ በማተኮር ወደፊት ልትቀጥሉ የሚገባችሁ አይነት እንቅፋቶች ናቸው፡፡

ከላይ በተጠቀሱት የእንቅፋት አይነቶች መካከል የመለየታችሁ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በተጨማሪ እነዚህን አትርሱ፡-
1. ሁል ጊዜ አንድ ነገር ለመጀመር እቅድ ሰታወጡ በእቅዳችሁ ውስጥ ለድንገተኛውና ላልተጠበቀው እንቅፋት ማቀድን አትርሱ፡፡

2. ያልተጠበቀና ድንገተኛ እንቅፋት ሲያጋጥማችሁ ትክክለኛውን ምላሽ በመምረጥ ምላሽን ለመስጠት ሞክሩ፡፡

3. አንድ እንቅፋት ካጋጠማችሁና አስፈላጊውን ምላሽ ከሰጣችሁ በኋላ ወደ ዓላማችሁና ወደስራችሁ በመመለስ እሱ ላይ ማተኮርን አትርሱ፡፡
source:-Dr Eyob Mamo

Address

Konso

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wedaju Orkaido posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Wedaju Orkaido:

Share