06/03/2026
ቀን 17፡ ቁርጠኝነት እና በራስ መተማመን
ከነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዓ.ወ) ታላላቅ ባሕርያት አንዱ እርግጠኛ መሆን በሚከብድበት ጊዜያትም ቢሆን በመተማመን ጽኑ ውሳኔዎችን የማድረግ ችሎታቸው ነው። ቆራጥነት ለማንኛውም መሪ ወይም ባለራዕይ ወሳኝ ባህሪ ነው። ቆራጥነት ማለት ፍርድህን ስለማመን፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ምርጫ ስለማድረግ እና በእነሱ ላይ በእምነት መቆም ነው።
አነቃቂ ታሪክ፡-
በበድር ጦርነት ወቅት ነብዩ (ሶ.ዓ.ወ) አሳሳቢ ጊዜ ገጥሟቸዋል። የሙስሊሞች ቁጥር ከጠላቶቻቸው እጅግ ያነሰ እንዲሁም የነበራቸው ጥቂት የውጊያ መሳርያ፣ ግመሎች እና ፈረስ ሲሆን የጠላት ጦር በአንፃሩ ሦስት እጥፍ የወታደር ቁጥር የነበረው በደንብ የታጠቀ፣ ብዙ ፈረሶች እና ግመሎችንም ለውጊያ ያዘጋጀ ስለነበር ውጥረት ከፍ ያለበት ወቅት ነበር። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ባልደረቦቻቸውን አማከሩ፣ ምክር የመፈለግን አስፈላጊነት በማሳየት፣ ነገር ግን የሚወስኑበት ጊዜ ሲደርስ፣ ጸንጠው ቆሙ። በእምነት፣ በስልት እና በድፍረት በመተማመን ጠላትን ለመጋፈጥ ድፍረት የተሞላበት ምርጫ አደረጉ። የእሳቸው ቆራጥነት ወደ ድል ብቻ ሳይሆን ተከታዮቻቸው በችግር ጊዜ የራሳቸውን ችሎታ እንዲያምኑ አነሳስቷቸዋል።
ከዚህ ፅሁፍ ምን እንማራለን?
ከዚህ የታላቁ ነብይ(ሰ.በ.ይ) ታሪክ በእራስ በመተማመንን ውሳኔ ማሳለፍን ነው። በራስ መተማመን ማለት ሁሉንም መልሶች ማግኘት ማለት አይደለም። ባለህ እውቀት እና ሃብት የምትችለውን ምርጥ ውሳኔ ማድረግ እና በሂደቱ ላይ የመላመድ ችሎታህ ላይ እምነት ማድረግ ማለት ነው። ውሳኔ አለማድረግ ወደ መቀዛቀዝ ይመራል፣ ወሳኝ እርምጃ ግን አይበገሬ ኃይል ይፈጥራል።
የድርጊት መርሃግብር፡-
ዛሬ፣ ለሌላ ጊዜ ያራዘምከውን አንድ ጽኑ ውሳኔ አድርግ። ስለ ንግድህ፣ ስለግል ህይወትህ ወይም ራስን ማሻሻል ሊሆን ይችላል። እራስህን እመን፣ እርምጃ ውሰድ(ተንቀሳቀስ) እና የውጤቱ ባለቤት ሁን።
በል አትቀርዝዝ ተነሳ!
ሰበብ አምላኪ አትሁን!
እስከዛሬ የደረደርካቸው ሰበቦች ወደኋላ ጎተቱህ እንጂ ምን ጠቀሙህ?
የማሰላሰያ ጥቀስ፡-
"በእያንዳንዱ ችግር መካከል ዕድል አለ።" — አልበርት አንስታይን
ኢንጂነር ማክሲሚሊያን
ረመዳን ሙባረክ!