GMTC Ethiopia

  • Home
  • GMTC Ethiopia

GMTC Ethiopia Speak the truth, live for the glory of God, and serve those around you.

21/03/2026

!
እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ፤ እንዴት መጸለይ እንደሚገባን አናውቅም፤ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ በማይችል መቃተት ።
ልባችንንም የሚመረምረው እርሱ የመንፈስን ሐሳብ ያውቃል፤ ምክንያቱም መንፈስ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለቅዱሳን ይማልዳልና። ሮሜ 8:26-27

ከአይረሴዎቹ የቄስ ጉዲና ቱምሳ ንግግሮች መካከል ሁለቱን እነሆ:-"ገንዘብ ስለሰጣችሁን ግንኙነታችሁን የጌታና የባሪያና አይነት ልታደርጉ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ከእናንተ ጋር የጀመርነውን ሕብረት ...
22/02/2026

ከአይረሴዎቹ የቄስ ጉዲና ቱምሳ ንግግሮች መካከል ሁለቱን እነሆ:-

"ገንዘብ ስለሰጣችሁን ግንኙነታችሁን የጌታና የባሪያና አይነት ልታደርጉ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ከእናንተ ጋር የጀመርነውን ሕብረት ለማቋረጥ እንገደዳለን" | ከቄስ ጉዲና ቱምሳ ለሉተራን ዎርልድ ፌዴሬሽን (LWF) የተሰጠ የማስጠንቀቂያ ንግግር ነበር |

ደርግ ሊያጠፋው በዙሪያው ማንዣበብ በጀመረ ጊዜ የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ኔሬሬ አዲስ አበባ ኤርፖት አስጠርቶት "ወደ ታንዛንያ ይዤህ ሊህድ" ባለው ጊዜ የቄስ ጉዲና ቱምሳ ምላሽ ይህ ነው:- "በጎቼን ለማን ትቼ ነፍሴን ላድን እኮበልላለሁ?" የሚል ነበር። ለዚያ ለዚያማ አሜሪካ፣ ኖርዌይ፣ ስዊድን፣ ጀርመንና ዴንማርክም ምርጫዎቹ ነበሩ።

ከስር የምትመለከቱት ምስል ከሚመራው ምስኪን ሕዝብ ጋር ወርዶ መሬት የተቀመጠው ቄስ ጉዲና ቱምሳ ነው። እንዳለውም በሕዝቡ መካከል ሰማዕት ሆኖ በክብር ያለፈ፣ ስሙም በክብር ሲወሳ የሚኖር እውነተኛና አይረሴው የወንጌል አርበኛ ነው.!

14/05/2018 ዓ.ም
22/01/2026

14/05/2018 ዓ.ም

22/01/2026

!
የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና፤ በሁለት በኩል ስለት ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፤ ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ዘልቆ ይወጋል፤ የልብንም ሐሳብና ምኞት ይመረምራል።
ዕብራውያን 4:12

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x) የፍቅርን ጌታ እያመለክን የፍቅርን ወንጌል እየሰበክን መኖር ስንችል ተዘልለን ጠላት በዘዴ ሥራ ሰጠን ፍቅርን አሳዶ ጥልን...
20/01/2026

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል
መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)

የፍቅርን ጌታ እያመለክን
የፍቅርን ወንጌል እየሰበክን
መኖር ስንችል ተዘልለን
ጠላት በዘዴ ሥራ ሰጠን
ፍቅርን አሳዶ ጥልን አንግሶ
በዓለም መድረክ ወንድሙን ከሶ
ቢያዜም ቢጸልይ እንዳይቀር ወጉ
ማን ተባረከ እስኪ ፈልጉ

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል
መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)

የራሱን ሰርቶ የሌላውን ሊያፈርስ
አንዱ በሌላው ከንፈሩን ሲነክስ
ጠላት ከኋላ ድንበር ሲገፋ
አርቆ አሳቢ አስተዋይ ጠፋ
ጌታ ኢየሱስ የሞተላቸው
በጐቹ ሁሉ የእርሱ ናቸው
በማን ርስት ነው የምንጣላው
እንመለስ ፍርድ አለ ኋላ

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል
መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)

በአንድ ቤት ማደር ቢያቅታቸው
አብርሃምና ሎጥ ቤተሰብ ናቸው
ችለው የለም ወይ ግራ ቀኝ መሄድ
ከማን ተማርነው ወገን ማሳደድ
ለምንኖርባት ለዚህች ምድር
ተስፋዋ ማነው ያለእግዚአብሔር
ፍቅርና ብርሃን በእኛ ከጠፋ
በቃ አለቀላት የላትም ተስፋ

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል
መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)

ፍቅር ርቦናል ፍቅር ጠምቶናል
ነገር ክርክር አንገላቶናል
እናንት አባቶች ፍቅርን መግቡ
ከተስፋው አገር በሰላም አግቡ

አዝ፦ ምድር ሰፊ ናት ምን ያገፋፋናል
መነካከሳችን ያጠፋፋናል (2x)

04/01/2026

ከስብከት ይበልጣል ልጅነት
‎ከመዝሙር ይበልጣል ልጅነት
‎ከትንቢት ይበልጣል ልጅነት
‎ከሁሉ ይበልጣል ልጅነት
‎የመስቀሉ ትልቁ ዋጋ
‎ ልጅነትህን እንዳትዘነጋ)(2)
‎ከስብከት ይበልጣል ልጅነት
‎ከመዝሙር ይበልጣል ልጅነት
‎ከትንቢት ይበልጣል ልጅነት
‎ከሁሉ ይበልጣል ልጅነት
‎የመስቀሉ ትልቁ ዋጋ
‎ልጅነትህን እንዳዘነጋ(2).

‎የህይወት መለኪያ አይደለም መዘመር
‎ወይ ነብይ ተብሎ ትንቢትን መናገር
‎ሁሉም ለምድር ነው ሁሉ በምድር ያልፋል
‎የእግዚአብሔር ልጅነት ሁሉም ይበልጣል
‎ኃጥእም ወደፊት ይስራው ፃዲቅ ወደፊት ይፅደቅ
‎ለሁሉም እንደየስራው ዋጋ አለው የሚከፈለው
‎አንተ ግን በልጅነትህ ላይ አንዳትቀልድበት
‎የጌታ ደም አለበት
‎አንተ ግን በልጅነትህ ላይ አንዳትቀልድበት
‎የጌታ ሞት አለበት
‎.
‎.
‎ያለ ሀብት ንብረቱን ከአባቱ ተካፍሎ
‎ገንዘብ ይዞ ወጣ ልጅነቱን ጥሎ
‎ሁሉ ከእጁ አልቆ ሁሉ ባዶ ሲሆን
‎ያአባቱ ቤት ትዝ አለው ያጣ ልጅነቱን
‎አንተ ግን በልጅነትህ ላይ አንዳትቀልድበት
‎የጌታ ደም አለበት
‎አንተ ግን በልጅነትህ ላይ አንዳትቀልድበት
‎የጌታ ሞት አለበት
‎ከስብከት ይበልጣል ልጅነት
‎ከመዝሙር ይበልጣል ልጅነት
‎ከትንቢት ይበልጣል ልጅነት
‎ከሁሉ ይበልጣል ልጅነት
‎የመስቀሉ ትልቁ ዋጋ
‎ልጅነትን እንዳትዘነጋ
‎.
‎.
‎እውነት ተገለጠ የደኽንነት ምስጢር
‎ጥበብ የተባለው በአብ ዘንድ የነበር
‎የከበረው ድንጋይ የማዕዘን ራስ
‎ስለ እኔ ልጅነት የሞተው ኢየሱስ
‎የእግዚአብሔር ልጅነት ሁሉም ይበልጣል

ዘማሪ አስፋው መለሰ
‎.

 #የቀጠለ ጊዜው ከዚህ በላይ ሳይረፍድ፣ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በ"ዶክትሬት" ዲግሪ ማከፋፈያ ሱቆች ላይ መነጋገር ግድ ይላል።በግሌ፣ "ካውንስል" በሚባለው ተቋም ላይ እምነት ባይኖረኝም...
31/12/2025

#የቀጠለ
ጊዜው ከዚህ በላይ ሳይረፍድ፣ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ በ"ዶክትሬት" ዲግሪ ማከፋፈያ ሱቆች ላይ መነጋገር ግድ ይላል።

በግሌ፣ "ካውንስል" በሚባለው ተቋም ላይ እምነት ባይኖረኝም ያለፈው ቅዳሜ አንድ ዘመዴን ለማስመረቅ በተገኘሁበት የምረቃ መርኅ ግብር ላይ በክብር ዕንግድነት የተገኙት፣ የኢትዮጵጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል፣ የሥነ መለኮት ትምህርት ቤቶች መምሪያ ዳይሬክተር፣ ቄስ ዶ/ር ዘላለም ቸርነት ደረጉት ንግግርና ለተመራቂዎቹ በለገሱት ምክር ግና ልቤ ቅልጥ ብላለች። ዳሩ በዕለቱ የሥነ መለኮት ተቋሙን የሚመሩት ዶክተሮችም ሆኑ ቃለ እግዚአብሔር ያቀረበው መጋቢ ተመሳሳይ ቅኝት ያላቸው ሆነው በማግኘቴ ነፍሴ በሃሴት ተሞልታ ነው የዋለችው። የኢትዮጵጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ባሕር ላይ እንደተጣለ መረብ የሚበላውንም የማይበላውንም፣ ውበት ያለውንም የሌለውንም ፍጥረት በላዩ ሸክፎ መያዙን እንዳስብ ያደረገኝ እንዲህ የሚለው፣ የቄስ ዘላለም ቸርነት (ዶ/ር) ድንቅ ምክር ነው፦

"...የዛሬ ተመራቂዎች፣ ይኼ ቀን ዲግሪ የምትቀበሉበት ብቻ ሳይሆን የእውነትን ቃል በቅንነት የሚይዝና የሚጠብቅ አገልጋይ ለመሆን ቃል የምትገቡበት፣ ለዓመታት የደከማችሁበትን፣ የድካማችሁን ፍሬ ለላቀ አገልግሎት የምታውሉበት፣ ለዚህ መጠራታችሁንም የምታስቡበት ነው። አንደኛ፣ ለስሙ እንጂ ለስማችሁ እንዳትኖሩ ተጠርታችኋል። እኔነት በሚልቅበት በዚህ ዓለም ውስጥ ስትኖሩ፣ ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ስም የተሸከማችሁ እንደሆናችሁ አስታውሱ። እናንተ የራሳችሁ አይደላችሁም፣ በዋጋ ተገዝታችኋል። ወደ አገልግሎት ስትሰማሩ ሰዎች እናንተን አይተው እንዲደነቁ ሳይሆን የእርሱን ስም እንዲቀድሱ ሕይወታችሁ ህያው ደብዳቤ ይሁን!"

"ሁለተኛ፣ ለክብሩ እንጂ ለክብራችሁ እንዳትኖሩ ተጠንቀቁ። ብዙ ጊዜ ክብርን ከዝና ጋር እናደባልቃለን። ነገር ግን እውነተኛ ክብር የእግዚአብሔር የመገኘቱ ክብደት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ 'ማናቸውንም ነገር ብታደርጉ፣ ሁሉንም ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት' ይላል። ሁሌም የራሱን ክብር ለማጉላት እንደሚሻ ሰው አትሁኑ፣ ነገር ግን ኢየሱስን ለማንጸባረቅ እንደተዘጋጀ መስታወት ሁኑ! የራሳችሁን ክብር ለማሳየት ከፈለጋችሁ በከንቱ ትደክማላችሁ፤ የእርሱን ክብር ካንጸባረቃችሁ ግን ትታደሳላችሁ።"

ምክሩ ለዕለቱ ተመራቂዎች ቢሆንም እኔም አብሬያቸው "አሜን!" ብያለሁ። መርኅ ግብሩ እንደተጠናቀቀም ለቄሱ ምሥጋናዬን አቅርቢያለሁ፣ አክብሮቴንም ገልጫለሁ።

© ሽመልስ ይፍሩ

በዶክትሬት ዲግሪ  "ሱቆች" ላይ መነጋገር ግድ ይላል!! "በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስም በየቦታው የሚከፈቱ 'ኮሌጆች ' ተጠሪነታቸው ለማን ነው? ሥርዓተ ትምህርታቸውን የሚገመግምስ ተቋም...
31/12/2025

በዶክትሬት ዲግሪ "ሱቆች" ላይ መነጋገር ግድ ይላል!!

"በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስም በየቦታው የሚከፈቱ 'ኮሌጆች ' ተጠሪነታቸው ለማን ነው? ሥርዓተ ትምህርታቸውን የሚገመግምስ ተቋም አለ ይሆንን? በዚሁ ከቀጠልን በሚመጡት አስርት ዓመታት ሁሉም አገልጋይ ነኝ ባይ፣ ጴንጤ ፓስተር፣ 'ዶክተር እገሌ' በሚል ታፔላ የጊዜውን ነቢይና ሃዋርያ በሚያስንቅ መልኩ በመድረኮች ላይ ሲንጎማለሉ፤ በትዕይንተ መስኮቶች ሲሸልሉብን ማየታችንና መስማታችን አይቀሬ ነው!! መማሩ ባልከፋ ግን ምንድን ነው የሚማሩት? አስር ገፅ ጥናት፣ ሀተታና የመፍትሔ ሀሳብ መፃፍ የማይችል ሰው እንዴት ሦስተኛ ዲግሪን (PhD) አጠናቋል ይባላል? የወንጌላውያን የቤት ስራ ገና አልተነካም!!"

ከፍ ብሎ የተነበበውን የአስተዋይ ሰው ዕይታ ከነ አባሪው ጋዋን ያጋራን Abdi Kuma Saketa ነው። ሃሳቡን የቋጨውም፦ “ሁሉ የራሳቸውን ይፈልጋሉና፥ የክርስቶስ ኢየሱስን አይደለም።” በሚለው የፊልጵስዩስ ምዕራፍ 2÷ 21 ቃል ነው። ይህ ጉዳይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ በቤተ ክርስቲያንና በሃይማኖታዊ ተቋማት ዙሪያ ትልቅ መነጋገሪያ፣ አንዳንዴም የትችት ሰበብ እየሆነ ከመጣ ከረምረም ብሏል። በተለይ፣ በሀገራችን፣ ራሳቸውን "ነቢይ" እና "ሐዋርያ" ብለው በሚጠሩቱና እንደ ሃይማኖት መሪዎች በሚታዩ አንዳንድ ግለሰቦች ዘንድ መሪነት እና "ቅባት" ብቻውን በቂ እንዳልሆነ የማሰብ ዝንባሌ እየታየ መጥቷል።

"ዶክተር" የሚለው የትምህርት ማዕረግ በሕዝብ ዘንድ ተሰሚነትን፣ ምሁራዊ ግርማንና ልዩ ተቀባይነትን እንደሚያሰጥ ስለሚታመንበት ብዙዎች ራሳቸው ከዚህ ጎራ ለመመደብ በመከጀል ላይ ናቸው። ከፊሎቹም ጋዋኑን ለብሰው፣ "ዶ/ር ... እገሌ" ተሰኝተው ፎቷቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻቸው መለጠፍ ጀምረዋል። ባጭሩ መንፈሳዊነትን በዓለማዊ መመዘኛ የመለካት ዝንባሌ በእጅጉ እየተስፋፋ መጥቷል። ይኼን በውል የተገነዘቡ አንዳንድ መንፈሳዊ የትምህርት ተቋማት ደግሞ ዲግሪ የሚሸጡ ሱቆች ሆነዋል። ።

መቼም በአካዳሚክ ዓለም ዶክትሬት (PhD) ለማግኘት ለዓመታት የሚፈጅ ምርምርና ጥናት ያስፈልጋል። "የክብር ዶክትሬት"ም ቢሆን አንድ ሰው ለሰጠው ከፍተኛ ማኅበራዊ ወይም መንፈሳዊ አገልግሎት እውቅና የሚቸር ማበረታቻ ብቻ ነው። ሃሳቡ መልካም ነው። ችግሩ ግን አሁን ላይ "የትምህርት ዶክተርነት" በቀላሉ የሚደርቡት ካባ መሆኑ፣ "የክብር" ዶክትሬትም "የክብር" የሚለው ቃል ተረስቶ ክብሩ የተሰጣቸው ግለሰቦች እንደ እውነተኛ ምሁር ራሳቸውን በዚያ ማዕረግ እየጠሩና እያስጠሩ መገኘታቸው ነው። ከዚህም የተነሳ በአካዳሚክ ዲግሪና በክብር ዶክትሬት መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷል። የሃይማኖት ተቋማት ጉዳይ አይመለከተውም ካልተባለ በስተቀር ትምህርት ሚኒስቴር የክብር ዶትሬት ለመጠሪያነት ማዋልን በቅርቡ በይፋ መከልከሉ ይታወሳል።

ከዚህ በፊት በሌላ ልጥፌ እንዳነሳሁት፣ "የክብር ዶክትሬት" የተሰጠው ሰው፣ "ዶ/ር/ፓስተር/ ሐዋርያ እገሌ" ከመባል አልፎ፣ "እጩ የክብር ዶ/ር እገሌ" እስከመባልም ተደርሷል። ያስቃልም፣ ያሳዝናልም! "መስመር አስያዡ ማነው?" የሚለው ጥያቄ እንደተጠበቀ ሆኖ ይኼ ነገር ካሁኑ መስተካከል ካልቻለ ግን መዘዙ ብዙ ነው። እንዲህ ዓይነቱ የተሳሳተ መሻትም ሆነ ድርጊት ሁሉን ነገር ሳይለፉ በአቋራጭና በገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል አደገኛ መልዕት የሚያስተላልፍ፤ ክብርን ከትህትና እና ከመንፈሳዊነት በራቀ መንገድ መፈለግን የሚያለማምድ ትውልድ ገዳይ ተግባር ነው።
#ይቀጥላል ..

 ! 😭አንተ አንቺ ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ እናንተ ሁላችሁ የሞት ቅጣት ፍርድ ተፈርዶባችኋል። ለዚያውም የዘላላም ሞት። አሁን በምታነቡበት በዚህችው ሰዓት ከሞት ፍርድ በታች ናችሁ። ምክንያቱም...
15/12/2025

! 😭
አንተ አንቺ ይህንን ፅሁፍ የምታነቡ እናንተ ሁላችሁ የሞት ቅጣት ፍርድ ተፈርዶባችኋል። ለዚያውም የዘላላም ሞት። አሁን በምታነቡበት በዚህችው ሰዓት ከሞት ፍርድ በታች ናችሁ። ምክንያቱም የእናንተ ዘረመል ወይም DNA ሲጠና በውስጡ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ሀጥያት የሚባል የአመፅ ወንጀል ተገኝቷል። ይህንን ወንጀል የፈፀሙት ቅድመ አያቶቻችሁ የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አዳም እና ሔዋን ሲሆኑ በእነርሱ የዘር ግንድ ወይም genealogy በኩል እየተላለፈ ወደ እናንተ በመድረሱ እናንተም ተጠያቂ ሆናችኋል። እጅግ የሚያሳዝነው ይህንን የሞት ፍርድ በምንም አይነት መንገድ ማስቀረት የማይታሰብ መሆኑ ነው።
! 😄
የምስራች ደግሞ አለ ፤ እሱም ምንድነው ካላችሁ የዘላለም ሞታችሁን ሽሮ የዘላለም ሕይወት ሊሰጣችሁ የሚችል አዳኝ ተገኝቷል። እሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። ሞታችሁን ወደ ሕይወት የለወጠው እንዲሁ በቃል ተሻረ ብሎ ሳይሆን የናንተን ሞት እራሱ ሞቶ ነው። እሱ ሞቶ ወንጀላችሁ የሚጠይቀውን ቅጣት በሙሉ ተቀጥቶ ሞትንም ድል አድርጎ በመነሳት አሁን በሰማይ በልዑሉ ፈጣሪ ቀኝ ተቀምጦ "እናንተ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ" ብሎ በፍቅር ይጠራችኋል። ስለዚህ የሞት ፍርደኞች የሆናችሁ ሁላችሁም ፍርዳችሁን ለመደምሰስ የተፈጠረውን ታላቅ ዕድል መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እያበሰርኩ ከናንተ የሚጠበቀው ሞታችሁን የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታና አዳኛችሁ እንደሆነ ማመን ብቻ ነው።
#ማሳሰቢያ:- በኢየሱስ አምኖ ለመዳን ቀኑ ዛሬ ሰዓቱም አሁን ሲሆን ዕድሉ የሚቆየው እስትንፋሳችን በውስጣችን እስከሚቆይበት ጊዜ ድረስ ብቻ ነው። እንዲሁም ቀድማችሁ የዕድሉ ተጠቃሚ የሆናችሁ ለሌሎች በአካልም ሆነ በሚዲያ የምስራቹን እንድታበስሩ እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ያሳሳስባችኋል።
: መፅሐፍ ቅዱስ
ሐዋሳ ሀይቅ ዳር ቃ /ሂ /ቤተ ክርስቲያን #መሰረታዊ ክርስትና ትምህርት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል::

09/12/2025

and experience God’s peace, presence, and provision.(" አምላኬም እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሞላባችኋል።" (ፊል 4:19))

ነብይ ሱራፌል ዝምታውን ሰበረ!አሁን በማህበራዊ በየነ መረብ(Social Media) እየሆነ ያለውን ነገር የትምህርት ሚንስትር ዝም ሊል አይገባም። ምክንያቱም በመንግስት ትውልድን ለመገንባት ለ...
03/12/2025

ነብይ ሱራፌል ዝምታውን ሰበረ!
አሁን በማህበራዊ በየነ መረብ(Social Media) እየሆነ ያለውን ነገር የትምህርት ሚንስትር ዝም ሊል አይገባም። ምክንያቱም በመንግስት ትውልድን ለመገንባት ለሀገር እድገት እየተፈጸመ ካለው ፓሊሲ ጋር የማጋጩ በርካታ መርዛማ አካሔዳቸውን እየተስተዋለ ስለሆነ።
በግልጽ በአደባባይ አትማር፣ አትለወጥ፣ ሰግጥ፣። ደድብ፣ ፈምስ እያለ ስንፍናን በማስፋፋት በአንድ ሀገር በመንግስትም ፣ሀይማኖት፣ በቤተሰብም ለልጆች ለውጥ የሚለፋውን የሚንፋውን ልፋት የምንሰራውን ስራ ዋጋ ቢስ የሚያደርግና የሚያበላሽ ስራ እየተሰራ ነው። ይኸ ዝም ሊባል አይገባም። ትውልዱ ሀገር ተረካቢ ሰይሆን በተለያዩ ሱሶች አዕምሮው የደነዘዘ እንሆን Creativity የሌለውና ራሱን መግትና ማስተዳደር የማይችል እንዲሆን ያደርጋሉና።
በተለይም በሀገራችን አሁን እየተሸላለሙ ያሉ እርቃንነትን የሚያበረታቱ ፤ ወንድ ሆነው የሴት ልብስ ፣ ቦርሳ ይዘው ሲሸለሙ አይተናል ነገ ላይ ልጆቻችንም ይህ ነገር ስኬት መስሏቸው እነሱን ለመሆን ይጥራሉ። እነዚህ ግብረሰዶማዊነትን ለማስፋፋት ወይ ከሰይጣን ወይ ከሌላ ሀገር አጀንዳ ይዘው የመጡ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የክፉ መልእክተኞች ናቸው። ይሄ መርዛማ ክፉ ዘራቸው ሳይስፋፋ ሳያድግ ልንቃወመው ይገባል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ብዙ ያልተፈታ ችግር እሰሰካሁን ቢኖር ባትም ከእንደዚ አይነት ትውልድን የሚገድልና ሀገርን የሚያመክን ክፉ ገሬጣ አይበልጥም። ከዚህ የከፋ ምንም ነገር ስለሌለ።
መንግስት ለትውልድ ለውጥ ማለትም ከተለያዩ ሱሶች ወጣቶች እንዲወጡ ብዙ ስራ ሰርቷል ውጤታማም እየሆነ ነው። ነገር ግን በዚህ ጉዳይ አፋጣኝ እርምጃ ሊወስድ ይገባል።
ይህንን ነገር ግን እኔ እንደ አንድ የሀይማኖት መሪ ፣ ለትውልድ ግድ እንደሚለው ሰው ሀላፊነቴን በተቃውሞ እወጣለሁ። ይህንን ጉዳይ በማጋራት ለመጪው ለነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ድምጽ እንሁን!!
https://www.facebook.com/share/v/17m6fTrY6B/

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when GMTC Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Equipment Service?

Share